Mela Service (service.et)


ሀ. መላ ፕላትፎርም ምንድነው?

የተለያዩ አገልግሎት ፈላጊዎችን፣ አገልግሎት ሰጪዎችና ቴክኒሺያኖችን በአንድ ቦታ በማቀናጀት የሞያ ግብይት የሚካሔድበት ኦንላይን የገበያ ስፍራ ነው።


ለ. በሲስተሙ ላይ ምን ዓይነት አገልግሎት ይሠጣል?


- በዋናነት 8 category ሲኖረው በእያንዳንዱ ውስጥ subcategory እንዲሁም ዝርዝር service ይኖራቸዋል፦


1. Maintenance (ጥገና)


- የፍሪጅ 

- የቴሌቪዥን 

- የሞባይል ስልክ

- የኮምፒውተር 

- የፎቶኮፒ ማሽን

- የፕሪንተር

- የልብስ ማጠቢያ ማሽን

- የምግብ ማብሰያ ማሽን

- የቬንትሌሽን ማሽን

- የኤሌክትሪክ ጄኔሬተር

- የቤት መኪና

- ሞተር ሳይክል


2. Installation (ዝርጋታ)


- የኤሌክትሪክ መስመር

- የቧንቧ መስመር 

- የቆሻሻ ማስወገጃ መስመር

- ሳታላይት ዲሽ 

- ሲሲቲቪ ካሜራ

- የኮምፒውተር ኔትወርክ 


3. Building (ግንባታ)


- ኢንቲሪየር ዲዛየን 

- የግድግዳ ቀለም ቅብ

- የብሎኬት ስራ

- የድንጋይ ስራ

- የአፈር ስራ

- የብረታብረት ስራ

- የእንጨት ስራ

- የአልሙኒየም ስራ

- የጂፕሰም ስራ

- የሴራሚክ ስራ

- የመስታወት ስራ

- የአጥር ስራ

- የኮርኒስ ስራ

- ፓርቲሽን

- ስክላፕቸር


4. Cleaning (የፅዳት)


- የመኖሪያ ቦታ

- የንግድ ቦታ

- ስፔሻላይዝድ 


5. Shifting (ቤት የመቀየር)


- መኖሪያ ቤት

- ቢሮ ወይም ሱቅ


6. Catering (የምግብ ዝግጅት)


- የድግስ ብፌ

- እንግዳ መቀበያ

- ቀላል መዝናኛ 

- ፕራይቬት ሌግዠሪ


7. Beauty (የውበት ስራ)


- ማስዋብ 

- ማሳጅ

- ሙሽራ መፈሸን


8. Consultancy (የማማከር ስራ)


ይህ አገልግሎት ትንሽ ለየት ያለ ሲሆን በዘርፉ ከተመረቁ ግለሰቦች ሳይንሳዊ የሆነ ቀለል ያለ ምክር ከመውሰድ ጀምሮ፣ ዶክመንት ማዘጋጀት፣ ሶፍትዌር መስራት፣ ፕራይቬት ስልጠና መስጠት፣ ከፊልና ሙሉ ፕሮጀክት መያዝን ያካትታል።


- ሜዲካል

- ቢዝነስ

- ሕግ

- ፋይናንስ

- ማርኬቲንግ 

- ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ 

- ኢንጅነሪንግ 

- አርክቴክቸር 

- ኢንዱስትሪያል 

- ኒውትሬሽን

- አግሪካልቸር

- ስነ-ውበት

- ስፖርት

- ሙዚቃ

- ቋንቋ 

- ቪዡዋል አርት

- ቲያትሪካል አርት

- ናቹራል ሳይንስ

- ሶሻል ሳይንስ

- ቪዲዮግራፊ


ሐ. አገልግሎት ሰጪዎች እነማን ናቸው?


- በዘርፉ በቂ እውቀት ያለው

- የተሟላ የመስሪያ ቁሳቁስ ያለው

- ለሚቀበለው ስራ ኃላፊነት የሚወስድ 

- ቴክኒሻኖችን በስሩ የሚያስተዳድር 

- የፋይናንስ ጉዳዮችን የሚያስተዳድር 

- የመስሪያ ቦታና ፍቃድ ቢኖረው ይመረጣል 

- ሁልጊዜ ኦንላይን ሆኖ ስራ የሚጠብቅ

- እራሱም ቴክኒሺያን ሆኖ መስራት የሚችል


መ. ቴክኒሺያኖች እነማን ናቸው?


- ሞያው ያለው በፊደል ሐ የተጠቀሱትን የማያሟላ 

- ሲስተሙ ላይ በቀጥታ መመዝገብ አይችልም 

- በአገልግሎት ሰጪ ስር ሆኖ የሚሰራ

- ቤት ለቤት በመሔድ ስራውን የሚሠራ


ሠ. ደምበኞች እነማን ናቸው?


- አገልግሎቱ በሚሰጥባቸው ከተሞች የሚኖሩ ግለሰቦች፣ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ ወይም ኦላይን በማፕ ጠቁመው በሌላ ከተማ የሚኖሩ ሪሞት ሰርቪስ ፈላጊዎች ናቸው።


ረ. የአሠራር ሒደቱ ምን ይመስላል?

- ሲስተሙ የደንበኛውን ሎኬሽን ከጎግል ካርታ በመውሰድ አገልግሎት የሚሰጥበት ዞን ውስጥ መሆኑንና፤ በተጠቀሰው ዞን ውስጥ የሚሰጡትን አገልግሎቶች ይዘረዝራል።

- ደምበኞች ከአፕልኬሽናቸው ወይም ከድረገፁ በካታጎሪ ከተዘረዘሩት አገልግሎቶች ውስጥ አስቸኳይ ወይም የቀጠሮ ትዕዛዝ ያቀርባሉ፤

- በሲስተሙ የተዘረዘሩት አገልግሎቶች ካልተመቻቸው፤ ስራውን በዝርዝር ፅፈው ለአገልግሎት ሰጪዎች በጨረታ ያቀርባሉ፤ 

- አገልግሎት ሰጪው በተመደበበት ካታጎሪ ውስጥ ሲስተሙ የቀጥታ ትዕዛዙንም ሆነ ጨረታውን ያቀርብለታል።

- የቀጥታ ትዕዛዙን በማየት ይቀበላል ወይም ሪጄክት ያደርጋል፤ ለጨረታው ደግሞ ዋጋ ያቀርባል።

- በመተዳደሪያው እንደተገለፀው በእያንዳንዱ ሰርቪስ ላይ የተቀመጠው ዋጋ ሊጨምርም ሊቀንስም ይችላል፤ በሁለቱ ወገን ስምምነት የሚወሰን ይሆናል።

- ለጊዜው የክፍያ ሁኔታ ከስራው በሁዋላ Cash after Service  ሲሆን በቀጣይ የኦላይን ክፍያ ሲስተም ይካተታል።

- አገልግሎት ሰጪው ከደምበኛው ጋር ከተስማማ ቴክኒሺያን መድቦ ወይም እራሱ ቴክኒሺያን ሆኖ ስራውን ይጨርሳል።

- የመስሪያ ቦታ የደምበኛው መኖሪያ ወይም የአገልግሎት ሰጪው ወርክሾፕ ይሆናል፤ ይህም በትዕዛዝ ማቅረቢያ ወቅት የሚወሰን ይሆናል።

- ደንበኛው ስራው ሲያልቅ ለአገልግሎት ሰጪው ሬቲንግ ይሰጣል፤ ይህም ለቀጣይ ስራው እጅጉን ጠቃሚ ነው።

- የሲስተሙ አስተዳደር፣ አገልግሎት ሰጪ፣ ቴክኒሺያን፣ እና ደንበኛው በውስጥ መስመር ቻት ይገናኛሉ፤ የአንድን ስራ ፓዝና ስታተስ ሁሉም ያዩታል፤ አላስፈላጊ ጉዳዮች ሲከሰቱም በሕግና ደንብ የሚፈታ ይሆናል።

 

ሰ. መተግበሪያዎች እነማን ናቸው?


1. Mela Service - የደምበኛ አፕልኬሽን

2. Mela Provider - የአገልግሎት ሰጪ አፕልኬሽን

3. Mela Handy - የቴክኒሺያን አፕልኬሽን


ሸ. ደምብና መመሪያዎች ምንድናቸው?


በኢትዮጵያ የአሠሪና ሠራተኛ እንዲሁም የንግድ ሕግ በበላይነት የሚገዙት ሲሆን ይህን የአገልግሎት መስጫ ፕላትፎርም ለየት ባደረገ መልኩ የሚከተሉት የህግ ማኅቀፎች ተዘጋጅተው በዋናው ገፅ ላይ ተቀምጠዋል ፦


- Terms and agreement

- Privacy policy

- Cancellation policy

- Refund policy


ቀ. አገልግሎት ሰጪ ለመሆን ምን ያስፈልጋል?


ከላይ በፊደል ሐ የተጠቀሱትን መስፈርቶች ካሟሉ፤

ከሶስቱ አማራጮች በአንዱ መመዝገብ ይቻላል...

1. በ 09 74 31 30 17 ደውሎ መመዝገብ ወይም

2. https://t.me/melaservice - ላይ የአገልግሎት ሰጪን አፕልኬሽን በማውረድ መመዝገብ ወይም

3. https://service.et/provider/auth/sign-up   - ይህን ሊንክ ተከትሎ መመዝገብ

የኮሚሽን አገልግሎት እስከምንጀምር፤ የሰብስክሪፕሽን ፓኬጅ አማራጮችን በሚያስፈልግዎ መጠን መርጠው መጨረስ ሲሆን፤ አፕሩቫል እንዳገኙ ስራዎን ይጀምራሉ!


ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለግዎ (09 11 53 02 17)

GET ALL UPDATES & EXCITING NEWS

Subscribe to out newsletters to receive all the latest activity we provide for you